ቅዱስ ገብርኤል የሚውልበትና የእመቤታችን ዕለት

ሐምሌ 19 – 2009 (July 26, 2017) ረቡዕ ቅዱስ ገብርኤል የሚውልበትና የሚታሰብበት ቀን/ ዕለት
ከቀኑ 12፡30 ጀምሮ በጸሎተ ቅዳሴ፣ በትምህርትና በመዝሙር ታስቦ ይውላል
ሐምሌ 21 – 2009 (July 28, 2017) ዓርብ የእመቤታችን ዕለት
ከምሽቱ 17፡30 ሰዓት ጀምሮ የስብከተ ወንጌልና የዝማሬ መርሐ ግብር ይዘጋጃል

 

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ነገር ግን እያንዳንዱ እንደ ራሱ ድካም መጠን የራሱን ደመወዝ ይቀበላል፡፡ (1 ቆሮ. 3 ፥ 8)

የቅዱስ ገብርኤልን ዓመታዊ በዓል ከዋዜማው ጀምሮ በሰላም እንድናከብር የረዳን አምላክ የተመሰገነ ይሁንና ለበዓሉ አከባበር መሳካት በገንዘብ፣ በጉልበትና በሃሣብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጋችሁ እንዲሁም በልዩ ልዩ አገልግሎት ስትደክሙ የነበራችሁ ምእመናን በሙሉ በቤተ ክርስቲያናችን ስም ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

በዓላችን ሐምሌ 16 – 2009 (Julay 23, 2017) እሑድ በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ያለፈ ቢሆንም ሐምሌ 19 – 2009 (Julay 26, 2017) ረቡዕ ቅዱስ ገብርኤል የሚውልበትና የሚታሰብበት ቀን/ ዕለት በመሆኑ ቤርሆዳለን 44 (Bergsjödalen 44) በሚገኘው ቤተ ክርስቲያናችን ከቀኑ 12፡30 ጀምሮ በጸሎተ ቅዳሴ፣ በትምህርትና በመዝሙር ታስቦ ይውላል፡፡ በዕለቱም ቀሲስ ስብሐትና መምህር በየነ ስምዖን ይገኛሉ፡፡

እንዲሁም ሐምሌ 21 – 2009 (Julay 28, 2017) ዓርብ የእመቤታችን ዕለት መልአከ ሕይወት/ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ጌጡ የኋላእሸትና መምህር በየነ ስምዖን የሚገኙበት ከምሽቱ 17፡30 ሰዓት ጀምሮ የስብከተ ወንጌልና የዝማሬ መርሐ ግብር ይዘጋጃል፡፡

ስለዚህ በነዚህ ቀናት ማለትም

ሐምሌ 19 – 2009 (Julay 26, 2017) ረቡዕ ከቀኑ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ

ሐምሌ 21 – 2009 (Julay 28, 2017) ዓርብ ምሽቱ 17፡00 ሰዓት ጀምሮ

ከላይ በተጠቀሰው ቦታ በመገኘት ቅዳሴውን በማስቀደስ፣ የነፍስ ምግብ የሆነውን ቃለ እግዚአብሔር በመስማት፣ የመላእክት ምግብ የሆነውን ዝማሬና ምስጋና በኅብረት በመዘመር፣ የበረከት ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ በቤተ ክርስቲያናችን ስም ተጋብዛችኋል፡፡

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!

የየተቦሪ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤልና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን፡፡

የሐምሌ ገብርኤል ዓመታዊው በዓል

ሐምሌ 15 – 2009 (Julay 22, 2017) ቅዳሜ ከቀኑ 15፡00 ሰዓት ጀምሮ
ሐምሌ 16 – 2009 (Julay 23, 2017) እሑድ የቻለ ሌሊት በማኅሌት ያልቻለ ከጧቱ 07፡00 ጀምሮ
ሐምሌ 19 – 2009 (Julay 26, 2017) ረቡዕ ከቀኑ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ
ሐምሌ 21 – 2009 (Julay 28, 2017) ዓርብ ምሽቱ 17፡00 ሰዓት ጀምሮ

 

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ሐምሌ 16 – 2009 (Julay 23, 2017) እሑድ ብፁዕ አቡነ ኤልያስና ሌሎችም አባቶች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ካህናት በተገኙበት ቤርሆዳለን 44 (Bergsjödalen 44) በሚገኘው የየተቦሪ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤልና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ዓመታዊው የሐምሌ ገብርኤል በዓል ይከበራል፡፡ ለበዓሉ ተጋባዥ ከሆኑት እንግዶች መካከል መምህር በየነ ስምዖንና ዘማሪ ገብረ ዮሐንስ ገብረ ጻድቅ የሚገኙ ሲሆን ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን ያቀርባሉ፡፡

የዋዜማው መርሐ ግብር ሐምሌ 15 – 2009 (Julay 22, 2017) ቅዳሜ ከቀኑ 15፡00 ሰዓት ላይ የሚጀመር ሲሆን በዝማሬ፣ በዋዜማ ቁመትና በስብከተ ወንጌል ይከበራል፡፡

በተጨማሪም ሐምሌ 19 – 2009 (Julay 26, 2017) ረቡዕ የቅዱስ ገብርኤል ዕለት የተወሰኑ አባቶች ካህናትና አገልጋዮች በሚገኙበት ከቀኑ 12፡00 ጀምሮ በጸሎተ ቅዳሴ፣ በትምህርትና በመዝሙር በዓሉ ታስቦ ይውላል፡፡

እንዲሁም መምህር በየነ ስምዖንና ዘማሪ ገብረ ዮሐንስ ገብረ ጻድቅ ለአንድ ሳምንት እዚሁ መቆየታቸውን ምክንያት በማድረግ ሐምሌ 21 – 2009 (Julay 28, 2017) ዓርብ የእመቤታችን ዕለት ከምሽቱ 17፡30 ሰዓት ጀምሮ የስብከተ ወንጌልና የዝማሬ መርሐ ግብር ይዘጋጃል፡፡

ስለዚህ ይህን መልእክት የምታነቡ ምእመናን ሁሉ ለሌሎችም ምእመናን ይህንን መርሐ ግብር  በማሳወቅ ከላይ በተጠቀሱት የበረከት ቀናት ማለትም

ሐምሌ 15 – 2009 (Julay 22, 2017) ቅዳሜ ከቀኑ 15፡00 ሰዓት ጀምሮ

ሐምሌ 16 – 2009 (Julay 23, 2017) እሑድ የቻለ ሌሊት በማኅሌት ያልቻለ ከጧቱ 07፡00 ጀምሮ

ሐምሌ 19 – 2009 (Julay 26, 2017) ረቡዕ ከቀኑ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ

ሐምሌ 21 – 2009 (Julay 28, 2017) ዓርብ ምሽቱ 17፡00 ሰዓት ጀምሮ

ከላይ በተጠቀሰው ቦታ በመገኘት የነፍስ ምግብ የሆነውን ቃለ እግዚአብሔር በመስማት፣ የመላእክት ምግብ የሆነውን ዝማሬና ምስጋና በኅብረት በመዘመር፣ ማኅሌቱን በመቆም፣ ቅዳሴውን በማስቀደስ፣ ታቦቱ ሲወጣ በዕልልታና በጭብጨባ በማጀብ የበረከት ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ ቤተ ክርስቲያናችን የግብዣ ጥሪዋን ታቀርባለች፡፡

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!

የየተቦሪ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤልና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን

Gebre Yohannis mezmur በምስጋና