የሚያዝያ ጊዮርጊስ ዓመታዊ በዓል

እሑድ ሚያዝያ 22 (April 30) ብፁዕ አቡነ ኤልያስና ሌሎችም አባቶች በተገኙበት ይከበራል
በዋዜማውም ቅዳሜ ማታ ሚያዝያ 21 (April 29) ከ17፡30 ሰዓት ጀምሮ የዋዜማ ቁመትና የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር ይኖራል
እንዲሁም ሰኞ ሚያዝያ 23 (May 1) የጊዮርጊስ ዕለት ከጧቱ 8፡00 ጀምሮ ጸሎተ ቅዳሴው ከተካሄደ በኋላ ትምህርተ ወንጌል በአባቶች ይሰጣል

 

ሚያዝያ ጊዮርጊስ ዓመታዊ በዓል 

የዘንድሮው የሚያዝያ ጊዮርጊስ ዓመታዊ በዓል ቤርሾዳለን 44 በሚገኘው የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤልና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን እሑድ ሚያዝያ 22 (April 30)ብፁዕ አቡነ ኤልያስና ሌሎችም አባቶች በተገኙበት ይከበራል፡፡ አከባበሩም አባቶች ካህናት ሌሊቱን በማኅሌት ጧት በቅዳሴ አገልግሎታቸውን ከቀጠሉ በኋላ ትምህርተወንጌል ይሰጥና የቅዱስ ጊዮርጊስ ጽላት ከመንበረ ክብሩ ወጥቶ ሥርዓንግሡ የሚካሄድ ይሆናል፡፡  በዋዜማውም ቅዳሜ ማታ ሚያዝያ 21 (April 29) 1730 ሰዓትጀምሮ የዋዜማ ቁመትና የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር ይኖራል፡፡

እንዲሁም ሰኞ ሚያዝያ 23 (May 1) የጊዮርጊስ ዕለት ከጧቱ 800 ጀምሮ ጸሎተ ቅዳሴው ከተካሄደ በኋላ ትምህርተ ወንጌል በአባቶች ይሰጣል፡፡

 ስለዚህ ይህንን መንፈሳዊ ጥሪ የምታነቡ ሁሉ በተባለው ሰዓትና ቦታ ተገኝታችሁ የበዓሉ በረከት ተሳታፊዎች ትሆኑ ዘንድ በቤተ ክርስቲያናችን ስምተጋብዛችኋል፡፡

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ 

የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤልና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን