የመስቀል በዓል በድምቀት ተከበረ

በስዊድን ሀገር በጎተንበርግ ከተማ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች በደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።

በዓሉ በጸሎት ተጀምሮ ወረብ በማቅረብ ቀጥሎ አባቶች በተገኙበት በምርቃት ተባርኮ ደመራው በርቷል።

ምዕመኑም በዝማሬ በመታጀብ በደመራው ዙሪያ በማሸብሽብ በእልልታና ጭብጨባ አድምቀውት፣ የሚመጣውን የደመራ በዓል እንድንናፍቀው አድርገዋል።

እንደወትሮው ሁሉ የደብሩ ማጀት እንዳይጎድል ደፋ ቀና የሚሉት ምእመናን ጣፋጭ የበረከት ማእድ ለታዳሚው በማቅረብ በደስታ የረድኤቱ ተካፋይና አካፋይ ሆነው አምሽተዋል።

የዘመናት ጌታ ለዘላለም ይክበር ይመስገን። አሜን።

[flagallery gid=1]