ሞክሼ ፊደላት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

(ይህ ጽሑፍ ለመጀመሪያ ጊዜ በጉተንበርግ ሐምሌ 18 ለገብርኤል በዓል ቀርቦ፣ ኦስሎ ላይ ተጨማሪ ይዘቶች ታክለውበት በነሐሴ 23 ለተክለኃይማኖት በዓል የቀረበ እና በቅርቡ ሌሎች ማሻሻያዎች ተደርገውበት የተዘጋጀ ነው።)

በመጀመሪያ ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይግባውና ሞክሼ ፊደላት የሚባሉት በንባብና በንግግር ጊዜ ተመሣሣይ ድምፅ ያላቸው ሆነው ነገር ግን ሲጻፉ በቅርፆቻቸው የሚለያዩ ፊደላት ሲሆኑ እነዚህም ሃሌታው ፣ ሐመሩ ፣ ብዙኃኑ ፤ ንጉሡ ፣ እሳቱ ፤ እሳቱ ፣ ዓይኑ ጸሎቱ እና ፀሐዩ ናቸው፡፡

የዚህ አጭር ጽሑፍ ዋና፤ ዋና አላማዎችም የሚከተሉት ናቸው፡፡

1 ሞክሼ ፊደላትን አንዱን በሌላው ቦታ እየተኩ መጻፍ የሚያስከትለውን የትርጉምና የምሥጢር መፋለስ መጠቆም፤

2 እያንዳንዱ ፊደል/ ሆሄ የራሱ የሆነ ትርጉም እንዳለው በምሳሌ ማሳየት፤

3 ቢያንስ የቅዱሳን ስም ሲጻፍ ጥንቃቄ እንዲደረግ ማሳሰብ፤

4 ሞክሼ ፊደላት በያሬዳዊ የዜማ ምልክቶች ላይ ያላቸውን ሚና ማሳየት፤

5 የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ምክንያታዊነት መግለጽ ሲሆኑ ለጽሑፉ መነሻ የሆኑት ምክንያቶች ደግሞ፡-

ሀ) ሞክሼ ሆሄያትን/ ፊደላትን ጠንቅቆ ያለመጻፍ ችግር በዓለማውያኑ ዘንድ ብቻ ሳይሆን በግእዝ ጸሐፊዎችና በቤተ ክርስቲያን ሰዎችም ዘንድ አሁን አሁን ጎልቶ እየታየ ያለ ችግር በመሆኑ፡፡

ለምሳሌ የታተሙ መንፈሳዊ መጻሕፍት ውስጥ፤ የመዝሙር ጽሑፎችና ቪሲዲዎች ላይ፤ መንፈሳዊ ድረ ገጾች ላይ፤ ከአብያተ ክርስቲያናት የሚላኩ መግለጫዎችና ደብዳቤዎች ውስጥ፤ . . . ትክክለኛዎቹን ፊደላት/ ሆሄያት በቦታቸው ያለመጠቀም ችግር በብዛት ይታያል፡፡ በጣም ተጠንቅቀው የሚጽፉ እንዳሉም መዘንጋት የለበትም፡፡

እነዚህን ሞክሼ ሆሄያት ወይም ፊደላት እጅ እንደገባ በዘፈቀደ ያለቦታቸው እያቀያየሩ መጻፍ ደግሞ የትርጉምና የምሥጢር መፋለስ ከማስከተሉም በላይ ለምስጋና ብለን የምንጽፈው ለስድብ ለክብር ብለን የምንጽፈው ለውርደት የመሆን አጋጣሚም ይኖረዋል፡፡

በአንዲት ፊደል መቀየር ምክንያት ምን ያህል የተፋለሰና ተቃራኒ የሆነ ትርጉም እንሚከሠት የሚከተሉትን ሐረጎች/ ዓ. ነገሮች እንደምሳሌ ማየት ይቻላል፡፡

ብሐት ለእግዚአብሔር ⇒ ውፍረት/ ስባት ለእግዚአብሔር፡፡

የዓለም ድነት በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ሆነ ⇒የዓለም መደህየት በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ሆነ፡፡

ረቀ በሥጋ እምድንግል ⇒ ከድንግል በሥጋ ሰረቀ/ ወሰደ (ሰረቀ ብርሃን ⇒ የብርሃን መሰረቅ/ መወሰድ)፡፡

የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በል ⇒ የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ጣዖት

ሰብ ሰገል ከሩቅ ምሥራቅ መጡ ⇒ ሰባ (70) ጥበብ ከሩቅ ምሥራቅ መጡ፡፡

የክርስቶስ ትንኤ ⇒የክርስቶስ መከልከል (ነሳ ⇒ከለከለ)፡፡

ፊደሎቹ ሲስተካከሉ የሚሰጡት ትክክለኛ ትርጉም

 ስብት ለእግዚአብሔር ⇒ ምስጋና ለእግዚአብሔር፡፡

የዓለም ድነት በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ሆነ ⇒ የዓለም መዳን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ሆነ፡፡

ረቀ በሥጋ እምድንግል⇒ከድንግል በሥጋ ተወለደ/ ተገለፀ (ረቀ ብርሃን ⇒ የብርሃን መገለጥ/ መታየት)

የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በል ⇒ የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብር/ አከባበር

ሰብ ሰገል ከሩቅ ምሥራቅ መጡ ⇒ የጥበብ ሰዎች ከሩቅ ምሥራቅ መጡ፡፡

የክርስቶስ ትንኤ ⇒ የክርስቶስ መነሳት

ለ) ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ሞክሼ ፊደላት/ ሆሄያት በመማር ማስተማር ተግባር ላይ መሰላቸትን፣ መታከትንና መወሳሰብን አስከትለዋል፤ እንዲሁም በሥነ ጽሑፎቻችን ላይ የተዘበራረቀ የፊደላት አጠቃቀም እንዲከሰት አድርገዋልና ይቀነሱ እያሉ የሚከራከሩ ምሁራን ስላሉ ሲሆን እነርሱ እንደሚሉት እነዚህ ሞክሼ ፊደላት/ ሆሄያት ከተቀነሱ ደግሞ የትርጉምና የምሥጢር መፋለስ ከመከሠቱም በላይ ሌላው ዓለም ያላገኘው ትልቁ የቤተ ክርስቲያናችን ልዩ ሀብትና የስብሐተ እግዚአብሔር መፍሰሻ የሆነው ያሬዳዊ ዜማ በምልክቶቹ ላይ አደጋ ይደርሳል፡፡ ይህም ማለት ወጥ የሆነው የድጓው፤ የቅዳሴው፤ የሰዓታቱ፤ . . . የቤተ ክርስቲያናችን ዜማ ሁሉ ጎደሎ የሆነ ወይም የተወሰነው ክፍል ዜማው የማይታወቅ ይሆናል ማለት ነው፡፡

 ለምሳሌ

ተብሎ የተመለከተ ምልክት ሲገኝና ተብሎ ተመልክቶ ሲገኝ ዜማው ፈጽሞ የማይገናኝ ከመሆኑም በላይ አንዱ (የመጀመሪያው) ግእዝ ዜማ ሲሆን ሌላው (ሁለተኛው) ደግሞ እዝል ዜማ ነው፡፡

ማለት “ኢይፈርሆ” እንደሚባለው ግእዝ ዜማ አዚም ማለት ሲሆን ማለት ደግሞ “አንጺሖ” እንደሚባለው እዝል ዜማ አዚም ማለት ነው፡፡

 የሃሌታው ሀ፣ ሐመሩ ሐ እና ብዙኃኑ ኀ ትርጉምና ያላቸው ልዩነት

ሀ ብሂል ሀልዎቱ ለአብ እምቅድመ ዓለም ⇒ ማለት የአብ አኗኗሩ ከዓለም በፊት ነው፡፡

ሐ ብሂል ሐመ ወሞተ ወተቀብረ ⇒ ማለት ክርስቶስ ታመመ፣ ሞተ፣ ተቀበረ፡፡

ኀ ብሂል ኃያል እግዚአብሔር ⇒ ማለት እግዚአብሔር ኃያል ነው፡፡

ር ⇒ የተማረ፤ ሊቅ

ር ⇒ ይቅርታ/ ምሕረት ያገኘ

ዳን ⇒የአንድነት ደጋፊዎች (ተዋሕዶ)

ዳን ⇒ ጥቂቶች፤ አናሳዎች

ነት ⇒ ማጣት፤ መቸገር (ድነትንና ባለጠግነትን አትስጠኝ፤ ነገር ግን የሚያስፈልገኝን እንጀራ ስጠኝ፥፡፡ ምሳሌ 30 ፡ 8)

ነት ⇒ መዳን፤ መፈወስ (እንግዲህ ይህ የእግዚአብሔር ድነት ለአሕዛብ እንደ ተላከ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን፡፡ የሐዋ. ሥራ 28 ፤ 28)

ያ ⇒ የእግዚአብሔር ኅቡእ ስሙ ነው፡፡

ያ ⇒ ለጭነት የሚያገለግል የቤት እንስሳ፡፡

ያ ⇒ በወንዝ ዳር የሚበቅል ዛፍ፡፡ (የወንዝ አኻያ ዛፎች ይከብቡታል። ኢዮ. 40 ፤ 22)

የንጉሡ እና እሳቱ ትርጉምና ያላቸው ልዩነት

ሠ- ብሂል ሠረቀ በሥጋ ⇒ – ማለት ጌታ በሥጋ ተወለደ /ተገለጠ፡፡

ሰ- ብሂል ሰብአ ኮነ እግዚእነ ⇒ – ማለት ጌታችን ሰው ሆነ፡፡

ረቀ ⇒ ወጣ፤ ተገለፀ፤ ብቅ አለ፡፡

ረቀ ⇒ ሌባ መነተፈ፤ በድብቅ ወሰደ፤ የራሱ ያልሆነ ነገርን ወሰደ

ብሐት ⇒ ውፍረት/ሥባት                         ብሐት ⇒ ምስጋና

ለ⇒በጉሮሮው ኡህ፤ ኡህ አለ                        ለ ⇒ ሥዕልን/ ምስልን ሠራ

ትንኤ ⇒ መነሣት                                         ትንኤ ⇒ መከልከል – – – (የምሥጢር መፋለስ)፡፡

እሳቱ እና ዓይኑ ትርጉምና ያላቸው ልዩነት

አ- ብሂል አአኲቶ ወእሴብሖ ለእግዚአበሔር⇒– ማለት እግዚአብሔርን በፍጹም ልቤ አመሰግነዋለሁ፡፡

ዐ – ብሂል ዐርገ ሰማያተ እግዚእነ ⇒ – ማለት ጌታችን ወደሰማይ ወጣ/ ዐረገ፡፡

ል ⇒ የቅዱሳን መታሰቢያ የሚከበርበት ቀን

(ፋሲካም የሚባለው የቂጣ በል ቀረበ። ማር. 22 ፤ 1)

ል ⇒ አይሁድ ያመልኩት የነበረ የጣዖት ስም

(ለበል ያልሰገዱትን ሰባት ሺህ ሰዎች ለእኔ አስቀርቼአለሁ። ሮሜ 11 ፤ 4)

ሰብ ሰገል ⇒ የጥበብ ሰዎች (ሄሮድስ ሰብ ሰገልን በሥውር ጠርቶ ማቴ. 2 ፤ 7)

ሰብ ሰገል ⇒ 70 ጥበብ (ከዚህ በኋላ ጌታ ሌሎቹን ሰብ ሾመ፡፡ (ሉቃ. 10 ፤ 1)

ለ ⇒ ለመነ                      ሠለ ⇒ሥዕል ሳለ፤

መት⇒አገልጋይ፤ ባሪያ (አመተ ማርያም)

መት ⇒ 12 ወራት ከ5 ወይም ከ6 ቀናት (52 ሳምንታት ) ዓ. ም.

ሩቅ ⇒ ሩቅ ቦታ                   ሩቅ ⇒ ያልተከፈነ፤ ልብስ-የለሽ (ዕሩቅ ብእሲ)

ት ⇒ እጅግ ብዙ              መት ⇒ቁጣ፤ መቅሠፍት

(አቤቱ፥ በቍጣህ አትቅሠፈኝ፥ በመትህም አትገሥጸኝ። መዝ. 6 ፤ 1)

የጸሎቱ እና ፀሐዩ ፀ ትርጉምና ያላቸው ልዩነት

 ፀ ብሂል – ፀሐይ ጸልመ በጊዜ ስቅለቱ ለእግዚእነ፡፡ ⇒ ማለት – ጌታ በተሰቀለ ጊዜ ፀሐይ ጨለመ፡፡

በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ሐይ ይበራሉ። (ማቴ. 13 ፤ 43)

ጸ ብሂል – ጸጋ ወክብር ተውህበ ለነ፡፡ ⇒ ማለት – ጸጋ እና ክብር ለእኛ ተሰጠን፡፡

በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በሎት ጽኑ፡፡ (ሮሜ 12 ፤ 12)

ሞክሼ ፊደላትናያሬዳዊ የዜማ ምልክቶች ጥቂቶቹ እንደምሳሌ

⇒ ዓርገ መረ              ⇒ ብዙ

⇒ ተፈሥ                 ⇒ ፋሲካ ብ

⇒ ኢይፈር                 ⇒ አንጺ

⇒ ነገት                     ⇒ ድር

⇒ በክልኤ ዓ              ⇒ ደመና ልብ

ሐይ ብሩህ               ⇒ዘኢይልም

ረ ⇒ወመረ             ዘ ⇒ዘግ ወዘሥርዓት                ር ⇒ ር እግዚአብሔር

⇒ ይርቅ ኮከብ   ን ⇒ እምቅዱን                        . . . ል ⇒አውተ ሲ

ዮ ⇒ ረዮሙ           ጋ⇒ጋ ወጽድቅ                         ወ ⇒ ወንነ ወኃይልነ

 እነዚህ የዜማ ምልክቶች በሌላ ሞክሼ ፊደላት ቢቀየሩ በምልክቶቹ መሠረት ለማዜም አይቻልም ወይም ዜማው ይቀየራል፡፡

 እንደ መፍትሔ

1 ትክክለኛውን ፊደል በትክክለኛው ቦታ ለማስቀመጥ መጽሐፍ ቅዱስን መጠቀም፡፡ ለምሳሌ የምንጽፈውን ቃል የሚከተለው ሊንክ ላይ በመጻፍ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዴት እንደተጻፈ ማየት፡፡ http://www.amharicbible.org/

መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብር፤ መልክ፤ ድቃን፤ ታት፤ ዒየሡሥ ክርሥቶሥ ሉቃ ዋርያት። . . . ብሎ ጽፎ አያውቅም፡፡

2 የምንጽፈውን ነገር የቤተ ክርስቲያን አባቶች እንዲያርሙት ማሳየት፤

3 ዕድሉ ከተገኘ ሕዝብ በተሰበሰበበት አጋጣሚ ሁሉ በትምህርት መልክ በተደጋጋሚ ማቅረብ፤

4 በሀገር ደረጃ ከፊደል ቆጠራ ጀምሮ በሥርዓተ ትምህርት መልክ አዘጋጅቶ ትውልዱን ማስተማር. . .

 ማጠቃለያ

ሞክሼ ፊደላት/ ሆሄያት ያለቦታቸው ሲቀመጡ ትርጉምና ምሥጢር ያፋልሳሉ፡፡

ለምሳሌ በልና በል፤ ድነትና ድነት፤ ትንኤ ና ትንኤ . . . ፈጽሞ የተለያየ ትርጉም ነው ያላቸው፡፡

ሞክሼ ፊደላት እንደሌሎቹ ፊደላት የራሳቸው የሆነ ትርጉም አላቸው፡፡

ለምሳሌ የ ””፤ የ “” እና የ “” ትርጉም ፈጽሞ የተለያየ ነው፡፡

በግዴለሽነትና በዘፈቀደ ሞክሼ ፊደላትን ያለቦታቸው እያቀያየሩ መጻፍ ሥርዓት የሌለው ሥነ ጽሑፍ መፍጠር ይሆናል፡፡

ለምሳሌ በእንግሊዘኛው የአጻጻፍ ሥርዓት ካት(ድመት) ለማለት “Cat” ብለን እንጽፋለን እንጂ “Kat” ብለን አንጽፍም፡፡

ሲቪል ለማለትም “Civil” ብለን እንጽፋለን እንጂ “Sivil” ብለን አንጽፍም፡፡

በንግግር ብቻ ሳይሆን በጽሑፎቻችንም ላይ ለቅዱሳኑ ስም ክብር መስጠት ተገቢ ነው፡፡

ለምሳሌ እግዚአብር ተብሎ የሚጻፈውን እግዚአብር/ እግዚብሄር/ ግዚአብር ብሎ አለመጻፍ፡፡

ላሴ ተብሎ የሚጻፈውን ላሴ/ / ላሤ ብሎ አለመጻፍ፡፡

አባቶች የቅዱሳኑን ስም ለማክበር ፊደሎቹን ከመጠንቀቅም በላይ በቀይ ቀለም አድምቀው (ቦልድ አድርገው) ይጽፉታል፡፡

በእንግሊዘኛው የአጻጻፍ ሥርዓት እንኳን “God” ማለት አምላክ ሲሆን god ማለት ደግሞ ጣዖት ማለት እንደሆነ ይታወቃል፡፡

ሞክሼ ፊደላት ቢወገዱ/ ቢቀነሱ የትርጉም መፋለስ ብቻ ሳይሆን እንዚህን ሞክሼ ፊደላት የማያውቅ ትውልድ ሲመጣ አባቶቹ በነዚህ ሞክሼ ፊደላት በመጠቀም ጽፈው ያስቀመጡለትን ነገር መጽሐፍ ቅዱስን ጨምሮ አንብቦ ለመረዳትና ለመመርመር ይቸገራል፡፡ ስለዚህ ግራ መጋባትና ታሪኩን ያለማወቅ ችግር ይገጥመዋል ማለት ነው፡፡

ሞክሼ ፊደላትን መቀነስ/ ማጥፋት ያሬዳዊ የዜማ ምልክቶችን መቀነስ/ ማጥፋት ማለት ነው፡፡ ብሎም ከስድስተኛው መጀመሪያ መ.ክ.ዘ. ጀምሮ የነበረውን የቅዱስ ያሬድ ዜማ መቀነስ/ ማጥፋት ሲሆን ከዚያም ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገረ የቆየውን የቤተ ክርስቲያን የምሥጋና ሥርዓት ማጥፋት/ ማፍረስ ይሆናል ማለት ነው፡፡

ስለዚህ ዛሬ ተነስቶ ሞክሼ ፊደላትን/ ሆሄያትን መቀነስ ሳይሆን አባቶቻችን ያለምክንያት ጠብቀው አላቆዩልንምና በተቻለ መጠን አጠቃቀማቸውን ለይተን በማወቅ ልንጠቀምባቸው ይገባል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል አሜን

መልአከ ኃይል ቀሲስ ታደሰ ጥበቡ

መስከረም 2008

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *