የመስቀል በዓል በድምቀት ተከበረ

በስዊድን ሀገር በጎተንበርግ ከተማ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች በደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።

በዓሉ በጸሎት ተጀምሮ ወረብ በማቅረብ ቀጥሎ አባቶች በተገኙበት በምርቃት ተባርኮ ደመራው በርቷል።

ምዕመኑም በዝማሬ በመታጀብ በደመራው ዙሪያ በማሸብሽብ በእልልታና ጭብጨባ አድምቀውት፣ የሚመጣውን የደመራ በዓል እንድንናፍቀው አድርገዋል።

እንደወትሮው ሁሉ የደብሩ ማጀት እንዳይጎድል ደፋ ቀና የሚሉት ምእመናን ጣፋጭ የበረከት ማእድ ለታዳሚው በማቅረብ በደስታ የረድኤቱ ተካፋይና አካፋይ ሆነው አምሽተዋል።

የዘመናት ጌታ ለዘላለም ይክበር ይመስገን። አሜን።

[flagallery gid=1]

ሞክሼ ፊደላት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

(ይህ ጽሑፍ ለመጀመሪያ ጊዜ በጉተንበርግ ሐምሌ 18 ለገብርኤል በዓል ቀርቦ፣ ኦስሎ ላይ ተጨማሪ ይዘቶች ታክለውበት በነሐሴ 23 ለተክለኃይማኖት በዓል የቀረበ እና በቅርቡ ሌሎች ማሻሻያዎች ተደርገውበት የተዘጋጀ ነው።)

በመጀመሪያ ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይግባውና ሞክሼ ፊደላት የሚባሉት በንባብና በንግግር ጊዜ ተመሣሣይ ድምፅ ያላቸው ሆነው ነገር ግን ሲጻፉ በቅርፆቻቸው የሚለያዩ ፊደላት ሲሆኑ እነዚህም ሃሌታው ፣ ሐመሩ ፣ ብዙኃኑ ፤ ንጉሡ ፣ እሳቱ ፤ እሳቱ ፣ ዓይኑ ጸሎቱ እና ፀሐዩ ናቸው፡፡

የዚህ አጭር ጽሑፍ ዋና፤ ዋና አላማዎችም የሚከተሉት ናቸው፡፡

1 ሞክሼ ፊደላትን አንዱን በሌላው ቦታ እየተኩ መጻፍ የሚያስከትለውን የትርጉምና የምሥጢር መፋለስ መጠቆም፤

2 እያንዳንዱ ፊደል/ ሆሄ የራሱ የሆነ ትርጉም እንዳለው በምሳሌ ማሳየት፤

3 ቢያንስ የቅዱሳን ስም ሲጻፍ ጥንቃቄ እንዲደረግ ማሳሰብ፤

4 ሞክሼ ፊደላት በያሬዳዊ የዜማ ምልክቶች ላይ ያላቸውን ሚና ማሳየት፤

5 የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ምክንያታዊነት መግለጽ ሲሆኑ ለጽሑፉ መነሻ የሆኑት ምክንያቶች ደግሞ፡-

Continue reading ሞክሼ ፊደላት